ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አረንጓዴ ለማድረግ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናወነ
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የበለጠ አረንጓዴና ውብ ለማድረግ ከታቀዱ የክረምት ወቅት መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ የሆነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም. በዩኒቨርሲቲው ተከናውኗል።
በመርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራንና ሠራተኞች፣ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች፣ የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ፈታኝ መምህራን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባለሙያዎች በንቃት ተሳትፈዋል።
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ በመቀጠል የዩኒቨርሲቲውን ገጽታ በሚያሻሽልና የበለጠ አረንጓዴ በሚያደርግ ሁኔታ እስከ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም. ድረስ ይከናወናል።
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲውን አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ፣ አካባቢን ለመጠበቅ እና የአካባቢ ጥበቃ ባህልን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ በተሳታፊዎች ከፍተኛ ተሳትፎና ቁርጠኝነት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።