ዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ውድመት ደርሶበት ላይነሳ ይችላል ሲባል በሚያስደንቅ ፍጥነት ተነስቶ በተለይ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሃገርና ለክልሉ ትልቅ ሃብት የሚሆን ማእከል መገንባቱ በጣም የሚደነቅ ነው።

የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር ፕረዚዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የተሰሩና በሂደት የሚገኙ ፕሮጀክቶች ጎብኝቷል። ፕረዚዳንቱ የዩኒቨርስቲው ኣይሲቲ መሰረተ ልማት፣ ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ አስተዳድር ህንፃ፣ ሆስፒታል፣ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ማእከልና ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ኮምፕሌክስ ህንፃዎች ላይ የአካል ምልከታ አድርገዋል።

ከጉብኝቱ ብኋላ ንግግር ያደረጉት ፕረዚዳንት ታደሰ እንደገለፁት ብዙ ዩኒቨርስቲዎች ኣይቻለው በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ያየሁት ግን ልዩና የሚያኮራ ስራ ነው።

ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ በወጣቶች የሚመራ መሆኑ በጣም አስደስቶኛል። በዩኒቨርስቲው ያለው ፈጣን እድገት የዛ ውጤት እንደሚሆን እገምታለሁ ሲሉም ተናግረዋል።

በጉብኙቱ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ

ዩኒቨርስቲው እየሰራው ያለው ስራ የሚያበረታታና ለህዝባችን ተስፋ የሚሰጥ ነው ሱሉ ተናግረዋል። ዓዲግራት ሆስፒታል ወስነን ለዩኒቨርስቲው መስጠታችን ደስተኞች ነን ሲሉም ኣክለው ገልፀዋል።

በመጨረሻም የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶ/ር ገ/ምክኤል ወ/ገብርኤል የትግራይ ግዜያት አስተዳደር ፕረዚዳንት በዩኒቨርስቲው እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች በአካል በመጎብኘታቸው አመስግነው የተሰጡን ገንቢ ሃሳቦች እንደ ግብዓት ተጠቅመን ለቀጣይ ስኬቶቻችን እንጠቀምባቸዋለን ብለዋል።