ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 220 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ከኢትዮ ቴሌኮም ተረከበ።
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎቹን በተጠናከረ መልኩ ለማስፈጸምና የመምህራንን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያገለግሉ 220 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ከኢትዮ ቴሌኮም በግዥ ተረክቧል።
የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት 220 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮቹ ለዩኒቨርሲቲው በይፋ ተላልፈዋል።
በርክክቡ ሥነ ሥርዓት ላይ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገብረሚካኤል ወልደገብርኤልን እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋል። ከኢትዮ ቴሌኮም በኩልም የሰሜን ሪጅን ከፍተኛ አመራሮች በሥነ ሥርዓቱ ተሳትፈዋል።
ዩኒቨርሲቲው ይህንን ግዥ በመፈጸም የዲጂታል ትምህርት፣ የመማር ማስተማር ሂደቶችን እና የአካዳሚክ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ እያከናወነው ያለውን ጥረት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ተገልጿል።
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ባለው ዓመት ከኢትዮ ቴሌኮም ለተመሳሳይ አገልግሎት የሚውል 230 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች መግዛቱ የሚታወስ ሲሆን ባጠቃላይ ለመምህራን የሚውሉ 450 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ተገዝተዋል።