በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት ተጀመረ!!
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን፣ እንዲሁም በክልሉ በተፈጠረው ሁኔታ ምክንያት ለጊዜው ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ መቀበሉ ይታወሳል።
ከዚህ በመቀጠልም በዩኒቨርሲቲው በሚገኙት ሰባቱም ኮሌጆች የሚገኙ የትምህርት ክፍሎች መደበኛውን የመማር ማስተማር ሂደት ጀምረዋል።
ከታች የተያያዙት ምስሎች በክፍል ውስጥ ያለውን የትምህርት ሂደትና በዩኒቨርሲቲው ግቢ የሚታየውን ወቅታዊ ድባብ ያሳያሉ።