በክልሉ በተፈጠረው ሁኔታ ምክንያት በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ለጊዜው ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ እንደቆዩ ይታወቃል።
ሆኖም ዩኒቨርሲቲው ባቀረበው ጥሪ መሠረት፣ ተማሪዎቹ ወደ ቀድሞ የትምህርት ተቋማቸው እየተመለሱ ይገኛሉ። ዛሬ በመጀመሪያው ዙር ወደ ዩኒቨርሲቲው የገቡ በርካታ ተማሪዎች በተማሪዎች ሕብረት አባላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የተማሪዎች ሕብረት ፕሬዚዳንት ሙሩፅ ብርሃነ እንደገለጹት፣ ዛሬ በመጀመሪያው ዙር የገቡትን ተማሪዎች ተከትሎ ነገና ከነገ ወዲያም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ወደ ግቢው እንደሚገቡ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ ተማሪዎቹ በቀድሞ የትምህርት ተቋማቸው ወደ ነበረው የትምህርት ሁኔታ እንዲመለሱ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ የምዝገባ ቀን በማራዘም ተማሪዎቻችን እንዲመጡ የዩኒቨርሲቲው አመራር ላደረገልን ድጋፍ በተማሪዎች ሕብረት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ውድ ተማሪዎቻችን፣ ወደ ሁለተኛ ቤታችሁ እንኳን በድጋሚ በደህና መጣችሁ!!