ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን ለሁለተኛ ቀን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለ ይገኛል!!

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም. ለሁለተኛ ቀን ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለ ይገኛል።

በአቀባበሉ ሥነ-ሥርዓት የዓዲግራት ከተማ ከንቲባ ኢ/ር ነጋሲ ተወልደን ጨምሮ ሌሎች የከተማው አስፈጻሚ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ግቢ ተገኝተው ለተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው በመልእክታቸው፣ የከተማው አስተዳደር ዩኒቨርሲቲው በሚፈልገው ሁሉም ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ፣ የከተማው አስተዳደር አመራሮች ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ በመምጣት ተማሪዎችን በደስታ መቀበላቸውን ያደነቁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገብረሚካኤል ወልደገብርኤል፣ ዩኒቨርሲቲውም እንደተለመደው ከከተማው ጎን በመቆም የሚያስፈልገውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲውና የከተማው ከፍተኛ አመራሮች የተማሪዎችን መመገቢያ ካፌ በመጎብኘት ከተማሪዎች ጋር የምሳ ማዕድ ተጋርተዋል።

ውድ ተማሪዎቻችን፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!!