ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም. በጠዋት መርሐ ግብር በርካታ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ ተቀብሏል።
የአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ከሰዓትም በተጠናከረ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን፣ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ እየገቡ ይገኛሉ። ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ጀምሮ ሌሎች አመራሮችም በመገኘት ተማሪዎቹን በደስታ እየተቀበሉ ይገኛሉ።
የአቀባበል መርሐ ግብሩ ነገ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም. የሚቀጥል ሲሆን፣ የአቀባበሉን ሂደት ተከታትለን መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
እንኳዕ ደሓን መጻእኩም! እንኳን ደህና መጣችሁ! Welcome!