በሃገር ደረጃ ለሚሰጠው መውጫ ፈተና ኣስመልክቶ በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጠ።
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) አስመልክቶ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ኣዘጋጀ።
በዓመቱ አጋማሽ የነበረ የመውጫ ፈተና በሃገር ደረጃ የተሻለ ውጤት እንደነበረና አሁንም ተደግሞ ለራሳችሁና ለዩኒቨርስቲው የምታኮሩ እንደምትሆኑ እተማመናለሁ ሲሉ የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተሩ ግርማይ ታደለ(ረ/ፕሮፌሰር) በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል።
በኦሬንቴሽኑ መርሃግብር ከፌደራል ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የመጣው ኣቶ ጥላሁን ደሰለኝ ተማሪዎች ወደ ፈተና አዳራሽ ሲገቡ ለፈተና በወጣ መመርያ መሰረት የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮችን በመለየት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፏል።
ተማሪዎች የማይፈቀዱ ነገሮችን በዶርም ትተው በመምጣት ፈተና በታቀደለት ግዜ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ ሓይሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው በፌደራል ፖሊስ ዋና ኢንስፔክተር መዝገቡ ጋሹ ገልፀዋል።
ከወዲሁ ለውድ ተማሪዎቻችን መልካም እድል እንመኛለን!!