ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በትራፊክ አደጋና በመንገድ ደህንነት ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት ጀምራል።

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በከተማው ለሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በትራፊክ አደጋና በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት የጀመረ ሲሆን በመጀመርያ ዙር ለፉነተ ብርሃን ተማሪዎች ሰጥቷል። ስልጠናው የተማሪዎችን የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ለማሳደግና የትራፊክ አደጋ መከላከል ባህልን ለማጠናከር ያለመ ነበር።

በስልጠናው ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራንና ባለሙያዎች እንዲሁም ከከተማው የህግ አስከባሪ አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል።

መድረኩን መ/ር ሃፍቶም ገ/ዮሃንስ ያስተዋወቁ ሲሆን፣ ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር መ/ር ፅጌ አሰፋ ናቸው። በንግግራቸውም የስልጠናውን ዓላማና ጠቀሜታ በማብራራት ተሳታፊዎች በመንገድ ደህንነት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ አሳስበዋል።

በዕለቱ መ/ር ተስፋይ ዘርኣይ በመንገድ ደህንነትና በትራፊክ አደጋ ዙሪያ ዝርዝር ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን፣ በተለይም የአደጋዎች መንስኤዎችና የመከላከያ መንገዶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ገዛኢ ስዩም እንደገለፁት፣ ይህ ዓይነቱ ስልጠና ለተማሪዎች እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ለቀጣይም በተቀናጀ ትብብር መሰል ፕሮግራሞችን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የከተማው መንገድ ደህንነት ተወካይ አቶ ፀሃየ ሓጎስ ተሳታፊዎችን በመቀበል ስለ መንገድ ደህንነት አስፈላጊነት ገለፃ ሰጥተዋል። እንዲሁም ኩማንደር በርሀ ሓድጉ በትራፊክ አደጋዎች ተፅዕኖና በቅድመ ጥንቃቄ አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ አቅርበዋል።