በክበረ በዓሉ ላይ የተገኙ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በተለይም የእምነቱ ተከታይ ለሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና ሠራተኞች የትንሳኤ በዓል የደስታ፣ የሠላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላቸው ልባዊ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ለተማሪዎች በተዘጋጀ የትንሳኤ ክብረ በዓል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ሃፍታይ ገ/የሱስ (ዶ/ር)፣የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ግርማይ ታደለ፣ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር መድሃንዬ መለስ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የትንሳኤ በዓልን በድምቀት በማክበራቸውና የዩኒቨርስቲው አመራሮች አብሮዋቸው በመዋላቸው የተሰማቸውን ልባዊ ደስታም ገልፀዋል ።
የብዓሉ አከባበር ድባብ ለማየት የፎቶ ማህደር ይመልከቱ
መልካም የትንሣኤ በዓል