የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለመምህራንና ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የሕፃናት ማቆያ (Daycare) አገልግሎት ለመስጠት በዩኒቨርሲቲው ግቢ እየተገነባ ያለውን ማዕከል ጎበኙ።
በጉብኝቱ የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንቶች ዶ/ር ገብረኪዳን ተስፋይ እና ፅጋብ አረጋዊ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እንዲሁም ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የሕፃናት ማቆያ ማዕከሉ ለብዙ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች የነበረ ጥያቄ በመሆኑ፣ ማዕከሉ በመጠናቀቅ ላይ ያለበትን ደረጃ በማየታቸው አመራሮቹ ደስታቸውን ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው የሥርዓተ ፆታና አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ይርጋለም ነጋሽ እንደገለጹት፣ የሕፃናት ማቆያ ማዕከሉ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፣ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በመጪው አዲስ ዓመት ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ገልጸዋል።
ማዕከሉ በመምህራንና በድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የሥራና የቤተሰብ ሃላፊነትን ለማመጣጠን እንዲሁም ለሠራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያግዝ አገልግሎት ይሰጣል።