ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድን ገመገመ

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተቋማዊ ዕቅድን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላትና ከከፍተኛ አመራሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል። መድረኩ የባለፈውን ዓመት የሥራ አፈጻጸም ለመገምገምና የመጪውን ዓመት ተቋማዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ያለመ ነው።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገብረሚካኤል ወልደገብርኤል በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ያለፈውን ዓመት የሥራ አፈጻጸም መገምገምና ለአዲሱ የበጀት ዓመት ዕቅድ ማውጣት የዩኒቨርሲቲውን ስትራቴጂያዊ ግቦች ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የተቋሙን ጥንካሬዎች በማስጠበቅ፣ ያሉ ክፍተቶችን በማረም፣ ግልጽ ዕቅድና ተጠያቂነት በማስፈን እንዲሁም ያሉ ሀብቶችን በብቃት በመጠቀም በትብብር መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድ የቀረቡት በስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህታ አለነ ነው። ተሳታፊዎችም በቀረበው ሪፖርትና ዕቅድ ላይ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና ምክረ ሐሳቦችን በማቅረብ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር በተሳታፊዎች ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቷል። በመጨረሻም የ2019 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድ ከተሳታፊዎች በቀረቡ ግብዓቶች እንዲጠናከርና በተሳካ ሁኔታ ወደ ትግበራ እንዲገባ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የ2ኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናወነ

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የበለጠ አረንጓዴና ውብ ለማድረግ ከታቀዱ የክረምት ወቅት መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ የሆነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ነሓሴ 07/2018 ዓ.ም. ለ2ኛ ዙር በዩኒቨርሲቲው ተከናውኗል።

በመርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚዳንት ዶ/ር ገ/ምክኤል ወ/ገብርኤል ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒቨርስቲው ካውስል አባላት ተሳትፈዋል።

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ በመቀጠል የዩኒቨርሲቲውን ገጽታ በሚያሻሽልና የበለጠ አረንጓዴ በሚያደርግ ሁኔታ እስከ ነሓሴ 15/2018 ዓ.ም. ድረስ የሚቀጥል ይሆናል።