አግኣዚ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምምድ እንዲያገኙ የተዘጋጀው የሞዴል ፈተና በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው።

አግኣዚ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ በ2018 ዓ.ም በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎች አስቀድመው በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምምድ እንዲያገኙ፣ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ቤቱ ደረጃ የተዘጋጀው የሞዴል ፈተና በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ነው።

Agazi General Secondary School, in collaboration with Adigrat University, is conducting a model examination prepared for the 2018 E.C. academic year. The initiative aims to provide Grade 12 students with practical experience in using technology before sitting for the national examination, which will be administered online in 2018 E.C. The model examination is currently being conducted at Adigrat University to help students become familiar with the online examination system and enhance their readiness.

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በትራፊክ አደጋና በመንገድ ደህንነት ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት ጀምራል።

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በከተማው ለሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በትራፊክ አደጋና በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ያተኮረ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት የጀመረ ሲሆን በመጀመርያ ዙር ለፉነተ ብርሃን ተማሪዎች ሰጥቷል። ስልጠናው የተማሪዎችን የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ለማሳደግና የትራፊክ አደጋ መከላከል ባህልን ለማጠናከር ያለመ ነበር።

በስልጠናው ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራንና ባለሙያዎች እንዲሁም ከከተማው የህግ አስከባሪ አካላት ተወካዮች ተገኝተዋል።

መድረኩን መ/ር ሃፍቶም ገ/ዮሃንስ ያስተዋወቁ ሲሆን፣ ፕሮግራሙን በይፋ የከፈቱት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር መ/ር ፅጌ አሰፋ ናቸው። በንግግራቸውም የስልጠናውን ዓላማና ጠቀሜታ በማብራራት ተሳታፊዎች በመንገድ ደህንነት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ አሳስበዋል።

በዕለቱ መ/ር ተስፋይ ዘርኣይ በመንገድ ደህንነትና በትራፊክ አደጋ ዙሪያ ዝርዝር ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን፣ በተለይም የአደጋዎች መንስኤዎችና የመከላከያ መንገዶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ገዛኢ ስዩም እንደገለፁት፣ ይህ ዓይነቱ ስልጠና ለተማሪዎች እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ለቀጣይም በተቀናጀ ትብብር መሰል ፕሮግራሞችን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የከተማው መንገድ ደህንነት ተወካይ አቶ ፀሃየ ሓጎስ ተሳታፊዎችን በመቀበል ስለ መንገድ ደህንነት አስፈላጊነት ገለፃ ሰጥተዋል። እንዲሁም ኩማንደር በርሀ ሓድጉ በትራፊክ አደጋዎች ተፅዕኖና በቅድመ ጥንቃቄ አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ አቅርበዋል።