ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለ ይገኛል!!
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበለ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ቀን በርካታ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ እየገቡ ይገኛሉ።
በአቀባበሉ ሥነ-ሥርዓት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገብረሚካኤል ወልደገብርኤልን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና የተማሪዎች ሕብረት አባላት በመገኘት ተማሪዎቹን በደስታ እየተቀበሉና “እንኳን ደህና መጣችሁ!” እያሉ ይገኛሉ።
የአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ዛሬ ጥቅምት 23 እና ነገ ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም. የሚቀጥል ሲሆን፣ ሁሉም ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲው በመምጣት እንዲመዘገቡ እናሳስባለን።