የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም. ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ አጸደቁ
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም. ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ በኮሌጁና በሆስፒታሉ አመራሮች፣ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተሳተፉበት የምክክር መድረክ አጸደቁ።
መድረኩን በይፋ የከፈቱት የኮሌጁና ሆስፒታሉ ሓላፊ በመወከል ዶ/ር አባዲ ኪ/ማርያም የ2019 ዓ.ም. ዕቅዱ የ2018 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ላይ በተደረገ ግምገማ በተገኙ ልምዶች፣ ጥንካሬዎችና ተግዳሮቶች ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ዕቅዱ የሰው ኃይል አቅምን ማጎልበት፣ የሠራተኞችን ተነሳሽነትና ተጠያቂነት ማሳደግ፣ የሆስፒታሉን አሠራር ዲጂታላይዝ ማድረግ፣ የጤና መረጃ ሥርዓትን ማጠናከር፣ የፋይናንስ ሀብትን በብቃት መጠቀም፣ የገቢ አቅምን ማሳደግ እና የጤና አገልግሎትና መሠረተ ልማት አቅምን ማስፋትን ያካትታል፣ ዘመናዊ መሳሪያዎች ማሟላት፣ የተገልጋይ እርካታ ከፍ ማድረግ ይገኙበታል።
በቀረበው ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና የማሻሻያ ሐሳቦች ቀርበዋል። የሆስፒታሉ ቺፍ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ጋይም ገ/ስላሴ፣ የአካዳሚክና ምርምር ዳይሬክተር ዶ/ር ጣሰው አብርሃ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ አቶ ገ/መድህን ሓጎስ ለተነሱት ጉዳዮች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የ2019 ዓ.ም. የሥራ ዕቅዱ በትብብር፣ በተጠያቂነትና በተቀናጀ አመራር በተግባር እንዲተረጎም አፅንዖት ተሰጥቷል። ዕቅዱም የተሻለ የጤና አገልግሎትና የተሻለ የሆስፒታል አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለመ ነው።