በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በገቢ ግብር አሰባሰብና አስተዳደር ዙሪያ የተሰጠውን ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።
ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ለ90 ተከታታይ ሰዓታት ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና በመጠናቀቁ፣ ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የማበርከት ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተወከሉ እንግዶች፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን እና ሰልጣኞች ተገኝተው ፕሮግራሙን አድምቀዋል።
በዚህ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ባደረጉት ንግግር፣ ስልጠናው ፈታኝና ጠንካራ ቢሆንም ተሳታፊዎችን ወደ ተግባራዊ ሥራ ለማሸጋገር እና የሙያ ብቃታቸውን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል። ተመራቂዎቹም ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር በማዋል ለሀገር ልማትና ለተቋማቸው እድገት እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።
በተጨማሪም የገቢዎች ሚኒስቴር ተወካይ ወ/ሮ ገነት ገብረመድህን ስለ ስልጠናው ዓላማ፣ የቆይታ ጊዜ እና የተገኙ ውጤቶች አጭር ማብራሪያ ሰጥተዋል። ስልጠናው ተሳታፊዎች በገቢ ግብር አስተዳደርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከተ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው፣ ፕሮግራሙ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል።