በዓዲግራት ከተማ የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከሰኔ 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ፈተና የቴክኒክ ችግር እንዳይገጥማቸው ትምህርት ቤቶቹ ለዩኒቨርስቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በዩኒቨርስቲው ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ በትምህርት ዘርፍ የሚደረግ ድጋፍ ለሃገርና ቤተሰብ ጠቃሚ የሚሆን ትውልድ ለማፍራት ትልቅ ሚና እንዳለው በማመን እስካሁን በአከባቢው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሰፋፊ ድጋፍ ስያደርግ ቆይቷል።
ሰኔ 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሚሰጥ ሃገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በዓዲግራት እና ኣከባቢው የሚገኙ በበይነ መረብ ፈተናቸው የሚወስዱ ተማሪዎች በፈተናው ወቅት የቴክኒክ ችግር እንዳይገጥማቸው የልምምድ ስራዎች በተከታታይ ቀናት እየሰሩ እንደሆነና የዩኒቨርስቲው የኣይሲቲ ባለሙያዎች ድጋፍ እያደረጉላቸው እንደሆነ የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ኣይሲቲ ዳይሬክተሩ ነጋሲ ታደሰ ገልፀውልናል።